
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው - ክብርት ዘቢባ መሀመድናስር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በዓል በሆሳዕና ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሐመድ ናስር አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በዓል በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት የዘንድሮውን በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል። የዘንድሮውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበርም ኃላፊዋ በመግለጫቸው አመላክተዋል። የዘንድሮውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል የተለየ የሚያደርገው በስራቸው ውጤታማ የሆኑ ሴቶች ያከናወኗቸው ተግባራት ለእይታ ይቀርባሉ ብለዋል። የፆታ እኩልነትን በማስፈን ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ መስኮችም እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የበአሉ መከበር ጉልህ ፋይዳ እንዳለውም ኃላፊዋ አስረድተዋል። በክልሉ በሁሉም መስክ የሴቶችን የአመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት ሚናቸውን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ ለዘርፉ ስኬታማነት የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚጠይቅም ኃላፊዋ በመግለጫቸው አመላክተዋል። በሀገሪቱ የተጀመረው የልማት እና የለውጥ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ይበልጥ መጎልበት አለበት ያሉት ኃላፊዋ በሁሉም ዘርፍ የመጡ ለውጦችን ፈጣንና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማረጋገጥ የተቀናጀ ትብብር እና ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል። በነገው እለት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል ላይ ለመታደም ከፌደራል እና ከክልል የተውጣጡ እንግዶች ወደ ሆሳዕና ከተማ እየገቡ መሆኑንም ኃላፊዋ አብራርተዋል። በመጨረሻም ለመላው ሴቶች እንኳን ለአለም አቀፍ የሴቶች ቀን(ማርች 😎 አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የበሴቶች የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን እኔዲወጣ የቢሮ ኃላፊዋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።