Skip to main content
news21

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማህበር ፅ/ቤት የረመዳን ጾም ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የአስቤዛ ድጋፍ አደረገ! ፅ/ቤቱ ዛሬ የክልሉ ሴቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ይርዳው በተገኙበት ለረመዳን ፆም የሚሆኑ የተለያዩ አስቤዛዎችን ድጋፍ አደርጓል። አሁን ያለውን የኑሮ ውድነትን ምክንያት በማድረግ ለረመዳን ፆም ድጋፍ የተደረገው አስቤዛ ዘይት፣ ዱቄት፣ የሾርባ እህልና ሩዝ ይገኙበታል፡፡ ድጋፉ በተደረገበት ወቅት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፎዚያ መሀመድ እንዳሉት ለታላቁ የረመዳን ወር እንኳን አደረሳቹህ በማለት ለረመዳን አስቤዛ የሚሆን እንደ መነሻ ዘይት ፣ዱቄትና የሩዝ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረጋቸውን አንስተዋል። እንደሚታወቀው የረመዳን ወር የመደጋገፍ የእዝነት ወር እንደመሆኑም መጠን ፣ያለው ለሌለው የመረዳደዳትና የመደጋገፍ ባህላችን እንዲያድግ ማድረግ በፈጣሪ ዘንድም ምንዳን የምንቋደስበት ስለሆነ ለአቅመ ደካሞች መርዳት ያስፈልጋል ብለዋል። ወ/ሮ ፎዚያ አያይዘው የሴቶች ማህበር የአቅም ችግር ያላበቸውን ሰዎችን በመደጋፍ ረገድ ከዚህ ቀደም ዘርፈ ቡዙ ተግባራትን ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱን ጠቅሰው የአቅም ውስንነት ላለባቸው ሰዎች መልካም መሆን ይበልጥ በረመዳን ሊደገም ይገባል ብለዋል።