Skip to main content
news20

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማህበር ፅ/ቤት በተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ያካሄደውን የድጋፍና ክትትል የመስክ ግብረ መልስ ገመገመ! የማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎች ከበለፈው ወር ጀምሮ የስድስት ወር አፈጻጸም መነሻ ያደረገ በክልሉ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በሴቶች ማህበር ታቅደው የተሰሩ ስራዎችን ምልከታ ማድረገቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ መነሻ የክልሉ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎች በድጋፍና ክትትል ወቅት የታዩ ጥንካሬዎችና ያጋጠሙ ውስንነቶችን በወራቤ ከተማ በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡ በጥንካሬና በጉድለት በመለየት ጥንካሬዎች እንዲቀጥሉና ጉድለቶችን በፍጥነት ለማረም የክትትልና ድጋፍ ስራ ወሳኝ እንደሆነ በውይይቱ ተገልጿል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፎዚያ መሀመድ እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል፡፡ አጠቃላይ የማህበሩን እንቅስቃሴ በሁሉም ዘርፍ ሴቶችን በልማት ህብረቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በግብርናው በጤናው በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የማህበሩን የገቢ አቅም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡዱንና በህብረት ስራ ማህበራት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ፕሬዝዳንቷ በዚህም በዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በተደረገው ድጋፍና ክትትልም ጥንካሬና ጉድለቶችን መለየት ተችሏል ብለዋል፡፡ እንደ ፕሬዝዳንቷ ገለጻ በድጋፍና ክትትሉ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ለማስቀጠል ፣መልካም ልምዶችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋትና ያጋጠሙ ውስንነቶችን በቀጣይ ለማሻሻል ስለመሆኑም ጠቁመዋል። ከዚህም መነሻ አጠቃላይ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የአባላት መዋጮ ለማጠናከር ለመቅረፍና የሴቶች ኢኮኖሚናዊ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት የቁጠባ ስራውን በተገቢው በቡድን እንዲቆጥቡ ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል። የማህበሩን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃቃሴ በቼክ ሊስት መሠረት በዞኖችና ልዩ ወረዳዎችን በተደረገው ድጋፍና ክትትል የተለዩ ጥንካሬዎችና ጉድለቶችን ያመላካታ ግብረ መልስ በስራ አስፈጻሚዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡