Skip to main content
news15

በተለያዩ ግዜያት ለሴቶች የሚሰጡ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን ወደተግባር በመቀየር በወጣትነት እድሜያቸው ላይ የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎችን በጥበብ አልፈው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባው የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዘቢባ መሀመድናር ገለፁ። በክልሉ በECM/FGM ፕሮግራም ከሚካሄድባቸው ዞኖችና የፕሮግራም ወረዳዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ስሰጥ የቆየው የህይወት ክህሎት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል። በስልጠናው ማጠቃለያ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ ክብርት ዘቢባ መሀመድናስር እንደገለፁት ለተከታታይ ቀናት በህይወት ክህሎት ማዳበር ላይ የተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ጠቃሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል። በተለይ ወጣት ሴቶችና ወንዶች በአፍላ እድሜያቸው ከሚደርስባቸው የተለያየ ጉዳት እራሳቸውን እንዲከላከሉና ለህይወታቸው ጠቃሚ የሆነ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲወስኑ ስልጠናው እንደሚያግዛቸውም አስገንዝበዋል። ሁሉም ሰልጣኞች ወደመጡበት አካበቢ ስመለሱ ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መነሻ አድርገው ማሰልጠን እንዳለባቸውም የቢሮ ኃላፊዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተለያዩ ግዜያት ለሴቶች የሚሰጡ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን ወደተግባር በመቀየር በወጣትነት እድሜያቸው ላይ የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎችን በጥበብ አልፈው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባውም ገልጸዋል። በተደጋጋሚ የሚሰጡ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች በወጣቶች ህይወት ተጨባጭ ውጤት ለመምጣት በተቀመጠው ግብ መሰረት የአሰልጣኞች ስልጠናው መሰጠቱን በቢሮው የሴቶች ተሳትፎና ንቅናቄ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታደሰ ተናግረዋል። የህይወት ክህሎት ስልጠናው በወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖሊቲካዊና ባህላዊ ዘርፎች የሚደርስባቸውን ጫና በማቃለል ተጠቃሚነታቸውን የሚያጎለብት እንደሆነም አክለዋል። በቢሮው በዩኒሴፍ የሚደገፉ ፕሮግራሞች አስተባበሪ አቶ ወ/ገብርኤል አኑሎ በበኩላቸው የህይወት ክህሎት አሠልጣኞች ስልጠና ለተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሶች በቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች ስሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል። በስልጠናው ሰልጣኞች ጥሩ እውቀት በመቅሰም በቀጣይ ሌሎችን እንዲያሰለጥኑ በሚያስችል አኳኃን ስልጠናው በጥሩ ዲስፒሊን መሰጠቱን አስረድተዋል። በስልጠናው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከልና በማስቆም ረገድ ሰልጠኞቹ በቂ ክህሎት እንዲያገኙ ስለማድረጉም አመላክተዋል። ወጣቶች የራሳቸውንም ሆነ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በስልጠና ያገኙትን ክህሎት ስራ ላይ ማዋል እንዳለባቸውም አቶ ወልዴ መክረዋል። ለተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሶች የተሰጠውን ስልጠና በጥሩ ትኩረትና ድስፒሊን በመከታተል ከስልጠናው ተገቢውን እውቀት ማግኘታቸውን ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል። እንዳየ መዋቅራቸው የተሰጣቸውን ስልጠና በአግባቡ ስራ ላይ ለማዋል እንደሚሰሩም ጠቁመዋል። በተለያዩ ርዕሶች ተዘጋጅቶ በቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና በተቀመጠው መርሐግብር መሰረት ለተከታታይ ቀናት በመስጠት ተጠናቋል።