Skip to main content
news12

"የሴቷ ጥቃ የእኔም ነው፤ ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የቆየውን የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀንን ምክንያ በማድረግ የተለያዩ አመራጮችን በመጠቀም በክልሉ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመሆን እየተሰሩ ነው። በዛሬው እለትም የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከዩ.ኤን.ኤፍ.ፒኤ ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ በሊሳና ከተማ በገበያ ላይ ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችንና ፆታን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችል የማስታወቂያ ስራ ከወረዳው ጋር በመሆን ተሰርቷል። በተለይ ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለእድሜ ጋብቻ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ አውቀው ከችግሩ እራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስራ ተሰርቷል።ቢሮው ከዩ.ኤን.ኤፍ.ፒኤ ጋር በመሆን የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀንን በማስመልከት በተለያዩ ቋንቋዎች የሬዲዮ ማስታወቂያ በማሰራት ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራንም ለተከታታይ ቀናት ስሰራ ቆይቷል። የሴት ልጅ ግርዛትና ያለእድሜ ጋብቻን ለማስቆም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ልወጣ ይገባል!!