Skip to main content
news8

በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ጥቃት አዳራሾች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል -የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር አለም አቀፍ የፀረ- ፆታዊ ጥቃት ቀን በዓል "የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው፤ ዝም አልልም!!" በሚል መሪ ቃል በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንዳሉት በሴቶችና ህፃናት የሚደርሱ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በቅንጅት ልንከላከላቸው ይገባል ብለዋል። ጥቃት እንዳይፈፀም ተከታታይነት ያለቸው የግንዛቤ ትምህርቶችን በመስጠት የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስና ተገቢውን ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል። በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፅሙ ጥቃቶች የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል። ጉዳቱን ለመከላከል እንደ ክልል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑ ጠቁመው በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ግዝ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ግዜ እየተከበረ የሚገኘው የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን በየደረጃው ሲከበር ቆይቶ የዛሬው ክልላዊ ማጠቃለያ በዓል እንደሆነ አክለዋል። የበዓሉ መከበር አላማው ወንዶች አጋርነታቸውን የሚያሳዩበትና ጥቃት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት እንደሆነም ተናግረዋል። ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በሴቶች ላይ የሚፈፀም አካላዊ፣ ወስባዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ አሊያም ሌላ ጉዳት ልያስከትል የሚችል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ስለመሆናቸውም ኃላፊዋ በንግግራቸው አብራርተዋል። በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መንስኤያቸውና የሚያስከትሉት ችግሮችም የፆታ እኩልነትን ከለመክበር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ድርጊቶቹን ለመከላከል የሁሉም ጥረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙት ጥቃቶች በጤናቸውና በህይወታቸው ከፍተኛ ችግር እያስከተለ ከመሆኑም ባለፈ ከቤተሰቦቻቸውና ከማህበረሰቡ ከማህበረሰቡ ጋር በሚኖራቸው ኑሮ ላይ ጫና እያሳደረባቸው እንደሆነም ገልጸዋል። በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ጥቃት አዳራሾች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። በበዓሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኤርሲኖ አቡሬ፣ የክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አክመል አህመዲንን ጨምሮ ሌሎች የክልል የዞንና ልዩ ወረዳ የዘርፉ ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።